=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
-<{አል-ቁርአን 46 : 15})>-
«ሰውንም ለወላጆቹ በጐ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው፤ በችግርም ላይ ሆና ወለደችው፤....»
-<({አል-ቁርአን 17:23-24})>-
(23) ጌታችሁም ከእሱ በቀር ያለን ነገር እንዳታመልኩ እና ለቤተሰቦቻችሁ ቅን ትሆኑ ዘንድ ደነገገ። በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው የእርጅና እድሜ በደረሱ ጊዜ <ኡፉ> አትበላቸው ፤ አትገላምጣቸውም። መልካምን ቃል ተናገራቸው።
(24) በእዝነት የውርደትና የሽንፈት ክንፍህን ዝቅ አድርግላቸው። እናም «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው» በል።
-<({አል-ቁርአን 29 : 8})>-
«የሰው ልጅ ለወላጆቹ መልካምና ታዛዥ ይሆን ዘንድ አዘዝነው። ነገርግን እውቀት በሌለህ ነገር በኔ ላይ እንድታሻርክ ቢጥሩ(ቢያስገድዱህ) አትታዘዛቸው፤...»
۵ በአህመድና በአነሳእይ እንደተዘገበው
ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ): ጀነት ከናታችሁ እግር ስር ናት ብለዋል።
ቡሐሪ መጽሐፍ 73, ጥራዝ 8, የሐ.ቁጥር 2
۵ አቡሑረይራ(ረ.ዐ) እንደተረከው
አንድ ሰው ወደ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መጣና ያረሱ ሉሏህ! በጣም ላገለግለው የሚገባ ማነው? ሲል ጠየቀ። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ሰውየው ቀጣዩስ ማነው? ሲል ጠየቀ። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ቀጣዩስ ማነው? ሲል በድጋሚ ጠየቀ። ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ለአራተኛ ጊዜ ቀጣዩስ ማነው? ሲል ጠየቃቸው። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አባትህ አሉት።
۵ በአቡ ዳውድና በኢብን ማጃ እንደተዘገበው
አቡ ኡሰይድ እንዳወራው
አንዴ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጋር ቁጭ ብለን ከሰላማህ ጐሳ የሆነ አንድ ሰው መጣና እንዲህ አላቸው:- የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ወላጆቼ ከሞቱ ብኻላ በኔ ላይ ሃቅ አላቸውን? ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:- አዎ! አሏህ በምህረቱና በእዝነቱ ይባርካቸው ዘንድ ዱአ ልታደርግላቸው ይገባል! ለሰዎች የገቡትን ቃልቂዳን አሟላ፤ ጓደኞቻቸውንና ዝምድናቸውን አክብር ብለዋል።
.♥.♥ማን እንደ እናት!!!♥.♥.
እናት የዛሬ ማንነታችን ስትሆን በመልካም ስብዕና ኮትኩታ ፣ ከመጥፎ ነገር ከልክላ አሳድጋናለች። የወደፊት ግባችን ምን መሆን እንዳለበት ሁሌም ትጨነቃለች ፣ ታልማለች። እሷ ሳትበላ እኛን ታጐርሳለች፤ የራሷን ስሜት ገድባ የኛን ታሟላለች። ስናለቅስ ልቧ በፍርሃት ፣ በጭንቀትና በትካዜ ይዋጣል። እሩቅ ቦታ ስንሄድ ሃሳቧ ሁሉ ጥቅልል ብሎ ስለኛ ደህነነት ማሰብና መጨነቅ ይሆናል። በምን ሁኔታ ላይ እንደሆን ዘወትር ትጠበባለች።
ታዲያ እናትን መገላመጥ መሳደብ በሷ ላይ መፎከስ ቀርቶ ኡፍ እንኴ ፈፅሞ ልንላት አይገባም። አይደለም እንዴ?
ይህን ሁሉ ፍቅር እዝነት ሰታን ልቧን መስበር ትልቅ ወንጀል ነው። እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እናታችነን በቅን መንፈስ እናገልግላት፤ እንከባከባት። የእናቱን ደስታ ፣ ፈገግታ ማየት የማይሻ ማን ይኖር ይሆን?
አሏህ በትንሹም ቢሆን የናታቸውን ሃቅ ከሚወጡት መካከል ያድርገን!!!
Websites:
http://youth-mission.mobie.in
http://youth-mission.blogspot.com
fb page:
http://facebook.com/youth.mission29
© ዝግጅት በአህመድ የሱፍ
2006
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|